የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ

9.1M5,000+
Pendidikan
3.0
የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ Screen Shot 0የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ Screen Shot 1

የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ

የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ ሲኖር ሁለት አይነት እውቀቶችን ይቀስማል ። እነዚህም መንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ እውቀት ናቸው ። ይህንን መፅሐፍ የተረጎምኩት Bible stories ከሚለው የሞባይል አፕሊኬሽን ነው ። ይህንን መፅሐፍ ለማዘጋጀት ያነሳሱኝ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ። አብዛኞቹ ሃይማኖቶች መልካም ስነ ምግባርን ይሰብካሉ ። እነዚህም መንፈሳዊ ፍቅርን ፣ ቤተሰብን ማክበር ፣ አለመዋሸት ፣ ለሰው ክፉ አለመመኘት ፣ አምላካችንን በፍፁም ልባችን ማመን እና መውደድ ፣ ሰውን መውደድ ፣ አለመስረቅ ፣ ሰነፍ አለመሆን ፣ ሰውን አለማማት ፣ ያለንን ማካፈል ፣ ሰውን አለመጉዳት ፣ ዝሙት አለ መስራት ፣ በሃሰት አለመመስከር እና የመሳሰሉት ናቸው ። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ህሊናችን የሚነግረን ነገሮች ናቸው ። እዚህ ላይ የክቡር ከበደ ሚካኤልን ግጥም ማስታወስ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ይህም ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም መፅሀፍ ቅዱስ ከላይ የጠቀስናቸውን ነገሮች ያስተምረናል ። ክርስቲያኖች መፅሐፍ ቅዱስን በየእለቱ ማንበብ እና በህይወታቸውም መተግበር አለባቸው ። ወላጆች ልጆቻቸውን መፅሀፍ ቅዱስን እንዲያነቡ እና እንዲተገብሩ ማበረታት አለባቸው ። ነገር ግን አብዛኞቻችን ይህንን አናደርግም ። በተጨማሪም በሀገራችን ለልጆች በሚመች መልኩ ከመፅሃፍ ቅዱስ ተወጣጥቶ የተፃፉ ብዙ መፅሀፍት የሉም ። አሁን ባለንበት ዘመን ልጆችን ወደተሳሳተ መንገድ የሚመሩ ነገሮች በዝተዋል ። ስለዚህ ስለ መንፈሳዊ ህይወት እና ስለ መልካም ስነምግባር ልጆችን ማስተማር በዚህ ግዜ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ። ይህ አፕሊኬሽን የተዘጋጀው በጥያቄ እና መልስ ጨዋታ መልክ ስለሆነ የተዘጋጀው አዝናኝ ነው ። አንድ ጥያቄ ስትመልሱ አስር ነጥብ ታገኛላችሁ ። አንድ ጥያቄ ስትሳሳቱ ሁለት ነጥብ ይቀነስባችሃል ። ጥያቄውን መመለስ ካልፈለጋችሁ "ይህ ጥያቄ ይለፈኝ ።" የሚለውን መምረጥ ትችላላችሁ ። ሁሉም ጥያቄዎች ምርጫ ናቸው ። ጥሩ ነጥብ ለማግኘት "የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርቶች ለሁሉም" የሚለውን አፕሊኬሽን ከ Google play store ላይ አውርዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ ። ወይንም መፅሐፍ ቅዱስን ማንበብ ትችላላችሁ ። ዋናው የዚህ አፕሊኬሽን አላማ ልጆች ስለ መፅሐፍ ቅዱስ እና ስነ ምግባር አጠቃላይ እውቀት እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው ። በተጨማሪም ልጆች መፅሃፍ ቅዱስን እንዲያነቡ ለማነሳሳት ይጠቅማል ። ውድ አንባቢያ ሆይ መፅሐፍ ቅዱስ በህይወትህ ከሚያስፈልጉህ ዋነኛው እና አንደኛው ነገር ነው ። ያለ እሱ ህይወት አስቸጋሪ ነው ። ለልጅህም ከምታወርሰው ትልቁ ስጦታ የመፅሀፍ ቅዱስን የሚያክል የለም ። ይህንን አፕሊኬሽን ሲጠቀሙ ጥሩ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈልጋል ። ይህንን አፕሊኬሽን ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍቱ ስሞትን ማስገባት አለቦት ። ይህ አፕሊኬሽን የመወያያ ገፅ አለው ። ይህ አፕሊኬሽን update ሳያስፈልገው ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ስለሚያስችል ከግዜ ወደ ግዜ አዳዲስ የተጨመሩ ነገሮች ሊኖሩት ስለሚችል በየተወሰነ ቀናት ኢንተርኔት ኮኔክሽን ከፍተን ከዚያ አፕሊኬሽኑን መክፈት ይመከራል ። ለምሳሌ የተጨመረ ክፍል ካለ ኢንተርኔት ከፍታችሁ ይህን የተጨመረውን ክፍል አፕሊኬሽኑ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ ። ይህንን አፕሊኬሽን ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍቱ ስሞትን ማስገባት አለቦት ።
Menampilkan lebih banyak

Apa yang baru

version 9.8

Informasi

  • ID:app1196249.vpd
  • Kategori:Pendidikan
  • Diperbarui:2020-09-16
  • Versi: kapan:9.8
  • Membutuhkan:Android 4.1